በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 29/2018 (ኢዜአ):- በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቦሌ ክፍለ ከተማን 3 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ መሳይ ተመስገን ሁለት ግቦችን ስታስቆጥር ረድኤት አስረሳኸኝ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች።
ውጤቱን ተከትሎ የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለት ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በስድስት ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል።
በሊጉ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቦሌ ክፍለ ከተማ በተመሳሳይ ስድስት ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ዛሬ በተደረገው ሌላኛው ጨዋታ መቻል አርባምንጭ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።