ቶተንሃም ሆትስፐርስ እና ማንችስተር ዩናይትድ ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
ቶተንሃም ሆትስፐርስ እና ማንችስተር ዩናይትድ ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 29/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ቶተንሃም ሆትስፐርስ እና ማንችስተር ዩናይትድ ያደረጉት ጨዋታ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
በቶተንሃም ሆትስፐርስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ማቲስ ቴል እና ሪቻርልሰን ግቦቹን ለስፐርስ አስቆጥረዋል።
ብራያን ምቡዌሞ እና ማቲያስ ዲልክት ለማንችስተር ዩናይትድ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ቶተንሃም ሆትስፐርስ እና ማንችስተር ዩናይትድ በተመሳሳይ 18 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው ሶስተኛ እና ሰባተኛ ደረጃን ይዘዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ ባለፉት ስምንት ጨዋታዎች ቶተንሃም ሆትስፐርስን ማሸነፍ አልቻለም።