ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መቻል ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 29/2018(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የአምስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር መቻል አርባምንጭ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ብርቄ አማረ በጨዋታ እና በፍጹም ቅጣት ምት የማሸነፊያውን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፋለች።

ውጤቱን ተከትሎ በሊጉ ሶስተኛ ድሉን ያስመዘገበው መቻል በ10 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አርባምንጭ ከተማ በአንድ ነጥብ የመጨረሻው 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በአሁኑ ሰዓት ቦሌ ክፍለ ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአበባ ቢቂላ ስታዲየም ጨዋታቸውን እያደረጉ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም