ቀጥታ፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 29/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአምስተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ባህር ዳር ከተማን 3 ለ 1 አሸንፏል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አቤል ያለው ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር አዲሱ አቶላ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

በረከት ጥጋቡ ለባህር ዳር ከተማ ብቸኛውን ግብ አስቆጥሯል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ በሊጉ ሶስተኛ ድሉን በማስመዝገብ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በዘጠኝ ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል።

በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ሽንፈቱን ያስተናገደው ባህር ዳር ከተማ በስድስት ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የቅዱስ ጊዮርጊሱ አቤል ያለው በሊጉ ያስቆጠራቸውን ግቦች ወደ አራት ከፍ በማድረግ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን መምራት ጀምሯል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም