የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ምልምል የፖሊስ ሰልጣኞችንና ዕጩ መኮንኖችን እያስመረቀ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ምልምል የፖሊስ ሰልጣኞችንና ዕጩ መኮንኖችን እያስመረቀ ነው
ቡልቡላ፤ ጥቅምት 29/2018(ኢዜአ)፡- የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምልምል የፖሊስ ሰልጣኞችንና ዕጩ መኮንኖችን ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት እያስመረቀ ነው።
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ በቡልቡላ መሰረታዊ ወታደራዊ የፖሊስ ማሰልጠኛ ማዕከል ያሰለጠናቸውን የመጀመሪያ ዙር ምልምል የፖሊስ ሰልጣኞችንና 2ኛ ዙር እጩ መኮንኖችን ነው በማስመረቅ ላይ የሚገኘው፡፡
ተመራቂዎቹ በስልጠና ቆይታቸው ልዩ ልዩ ፖሊሳዊ እውቀቶችንና ክህሎቶችን መቅሰማቸውም ተመልክቷል፡፡
እንዲሁም የማህበረሰቡን ሰላምና ደህንነት በማስጠበቅ የሚሰጣቸውን ተልዕኮና ግዳጅ በብቃት ለመፈፀም የሚያስችሉ ስልጠናዎች መውሰዳቸውም እንዲሁ፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የክልሉና የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎች እንግዶች እየተሳተፉ ነው፡፡