በብልፅግና እሳቤ የተቃኘ የገበያ ሥርዓት በመዘርጋት የምርት እና አቅርቦት ማዕከላት እየለሙ ነው - የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች - ኢዜአ አማርኛ
በብልፅግና እሳቤ የተቃኘ የገበያ ሥርዓት በመዘርጋት የምርት እና አቅርቦት ማዕከላት እየለሙ ነው - የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 29/2018(ኢዜአ)፦በብልፅግና እሳቤ የተቃኘ የገበያ ሥርዓት በመዘርጋት የምርት እና አቅርቦት ማዕከላት እየለሙ መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ገለጹ።
የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በአዲስ አበባ የልማት ሥራዎች ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።
በከተማዋ በተለያዩ ስፍራዎች እየተደረገ ባለው ጉብኝት በከተማዋ ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ምልከታ እየተካሄደ ነው።
የዜጎችን የቤት ጥያቄ ለመመለስ የተለያዩ የቤት ልማት አማራጮችን በመከተል ማለትም በመንግሥት ብድር፣ በበጎ ፈቃድ፣ በከተማ አስተዳደሩ በጀት፣ በግል ባለሀብቶች ብሎም በግልና በማኅበር ተደራጅተው ቤቶች እንዲለሙ በማስቻል የዜጎችን የቤት ጥያቄ ለመመለስ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።
እነዚህ የቤት ልማት ሥራዎች የቤት ጥያቄዎችን ከመመለስ ባሻገር ለዜጎች ማኅበራዊ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ሆነው መሠራታቸውም ተመላክቷል።
በብልፅግና እሳቤ የተቃኘ የገበያ ሥርዓት በመዘርጋት የምርት እና አቅርቦት ማዕከላት እየለሙ መሆኑም ተገልጿል።
እነዚህም የደላላን ሰንሰለትን በመበጠስ ዜጎች ከገበሬው በቀጥታ ምርት እንዲያገኙ በማስቻልና የኑሮው ውድነትን በመቀነስ ረገድ ጉልህ ሚናን እየተጫወቱ ነው።