ቀጥታ፡

የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ አመራሮች በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ

አዲስ አበባ፤ጥቅምት 28/2018 (ኢዜአ)፡-የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ አመራሮች በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

በምሥራቅ ሸዋ ዞን የቦራ ወረዳ ላይ እየተከናወነ ያለው የልማት ሥራ ከተጎበኙት መካከል ነው፡፡

በጉብኝቱ ላይ የታደሙት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)ብዝሃ ኢኮኖሚ አካሄድን መከተል መጀመራችን ብልፅግናን ለማሳካት ትክክለኛው መንገድ ላይ መሆናችንን ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡


 

በብልፅግና ሂደት ውስጥ ገጠሩን ማሸጋገርና ማዘመን ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ መሆኑን ያነሱት ኤርጎጌ (ዶ/ር)፥ አርሶ አደሩ ለፍጆታ ከማምረት በዘለለ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ሂደት ሚናው የጎላ ነው ብለዋል፡፡

በገጠር ትራንስፎርሜሽን ከማምረት ለውጪ ገበያ እስከማቅረብ የዘለቀ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

ገጠሩን ለኑሮ ምቹ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ስለመመልከታቸው የተናገሩት ሚኒስትሯ ገጠሩንና ከተማውን ለማስተሳሰር የተሄደበት ርቀት በጎ ጅምሮች መኖራቸውን ያመላከተ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም