በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሃዋሳ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሃዋሳ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 28/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ሃዋሳ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ በቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ስራ ይርደው እና ፀሐይነሽ ጁላ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ሃዋሳ ከተማ በውድድር ዓመቱ አራተኛ ድሉን በማስመዝገብ በ12 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። በአንጻሩ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ድሬዳዋ ከተማ በሶስት ነጥብ ከ10ኛ ደረጃ ወደ 11ኛ ዝቅ ብሏል።
የአምስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ ቀጥሎ ሲውል አዲስ አበባ ከተማ ከሸገር ከተማ ከቀኑ 7 ሰዓት፣ ልደታ ክፍለ ከተማ ከሊጉ መሪ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከቀኑ 9 ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይጫወታሉ።