ቀጥታ፡

ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገጾች መካከል አንዱ - ማዜ ብሔራዊ ፓርክ

202 ስኩየር ኪሎ ሜትር ስፋት ያለው ማዜ ብሔራዊ ፓርክ በ1997 ዓ.ም መመሥረቱን የፓርኩ ኃላፊ መስፍን ጭማ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል።

በብሔራዊ ፓርኩ ውስጥ 39 ትላልቅና መካከለኛ አጥቢ የዱር እንስሣት እና 80 የእፅዋት ዝርያዎች እንደሚገኙም ጠቁመዋል።

በተመሳሳይ 196 የአዕዋፍ ዝርያዎች በብሔራዊ ፓርኩ ውስጥ እንደሚገኙ በጥናት መረጋገጡንም ጠቅሰዋል።

ብሔራዊ ፓርኩ ለየት የሚያደርገው በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኘው የስዎን ቆርኬ መገኛ መሆኑም አስታውቀዋል።

የፓርኩን ደኅንነት ለመጠበቅ የጥበቃና ቁጥጥር ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉንና ለአካባቢው ነዋሪዎች በየጊዜው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና በመስጠት ለፓርኩ ደኅንነት ተባባሪ እንዲሆኑ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።

ይህን ተከትሎም ተጨባጭ ውጤቶች መገኘታቸውን አስታውቀዋል።

በ2017 ዓ.ም ከ500 በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች ፓርኩን መጎብኘታቸውን አንስተዋል።

ፓርኩ ለ44 ሠራተኞች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠሩን አቶ መስፍን ጭማ ጨምረው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም