ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በዓለም የጠረጴዛ ቴኒስ ሻምፒዮና  ትሳተፋለች 

አዲስ አበባ ፤ጥቅምት 27/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ በለንደን በሚካሄደው የዓለም የቡድን የጠረጴዛ ቴኒስ ሻምፒዮና በሴቶች ተሳትፎ እንደምታደርግ የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ። 

ሻምፒዮናው የዓለም አቀፍ የጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን የተመሰረተበትን 100ኛ ዓመት በማስመልከት ከሚያዚያ 20 እስከ ግንቦት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።   

በውድድሩ ላይ በሁለቱም ጾታዎች በአጠቃላይ 64 ቡድኖች ይሳተፋሉ። 


 

የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ የሴቶች ብሄራዊ ቡድን በዓለም የቡድን የጠረጴዛ ቴኒስ ሻምፒዮና እንደሚሳተፍ የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ገልጿል። 

ብሄራዊ ቡድኑ የሚሳተፈው እ.አ.አ በ2025 በነበረው ዓለም አቀፍ የጠረጴዛ ቴኒስ ደረጃ አማካኝነት መሆኑ ተመላክቷል።

ቡድኑ እ.አ.አ በ2024 በተካሄደው ሻምፒዮና ላይ ተሳትፎ አድርጎ ነበር። 

የኢትዮጵያ ተሳትፎ ለጠረጴዛ ቴኒስ ስፖርት እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም