ቀጥታ፡

አራተኛው ዓለም አቀፍ የማዕድንና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ በህዳር ወር በአዲስ አበባ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 27/2018(ኢዜአ)፦ አራተኛው ዓለም አቀፍ የማዕድንና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ (ማይንቴክስ ኢትዮጵያ) ከህዳር 4 እስከ 7 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ዓለም ዓቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል እንደሚካሄድ የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኤክስፖው ላይ የማዕድን አምራቾች፣ የማዕድን ላኪዎች እና ተጠቃሚዎች፣ የቴክኖሎጂ አምራቾችና አቅራቢዎች፣ ዓለም አቀፍ የማዕድን ዘርፍ ባለሀብቶች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የማዕድን ኩባንያዎች፣ የመንግስት ተቋማት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ይሳተፋሉ።

የኢትዮጵያን የማዕድን ዘርፍ እድሎች ማስተዋወቅ እና ኢንቨስትመንት መሳብ አላማ ያደረገው ኤክስፖ የዘርፉ ተሞክሮዎች እና የኢንቨስትመንት አማራጮች የሚቀርቡበት የፓናል ውይይቶች እንደሚካሄዱ የማዕድን ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

በየዓመቱ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ ኤክስፖ በየጊዜው የተሳታፊዎች ቁጥር እያደገ መምጣቱን ገልጾ፤ የማዕድን ቴክኖሎጂ አምራቾች ከማዕድን አምራቾችና ላኪዎች ጋር ምርትና አገልግሎታቸውን እንዲያስተዋውቁ እድል መፍጠሩን አመልክቷል።

የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ከፍተኛ ድርሻ እየተወጣ እንደሚገኝ በማንሳት።

ኤክስፖው እያደገ የመጣውን የማዕድን የወጪ ንግድ አፈጻጸም የበለጠ ለማሳደግ ያስችላል ነው ያለው ሚኒስቴሩ በመግለጫው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም