ቀጥታ፡

በሻምፒዮንስ ሊጉ ካራባግ እና ቼልሲ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 26/2018 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ መርሃ ግብር ካራባግ እና ቼልሲ ያደረጉት ጨዋታ ሁለት በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

ማምሻውን በቶፊክ ባህራሞቭ አዲና ሬስሪፐብሊክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሊያንድሮ አንድራዴ በጨዋታ እና ማርኮ ያንኮቪች በፍጹም ቅጣት ምት ለካራባግ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

እስቴቫኦ እና አሌሃንድሮ ጋርናቾ ለቼልሲ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ቼልሲ እና ካራባግ በተመሳሳይ ሰባት ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው 10ኛ እና 12ኛ ደረጃን ይዘዋል።

በሌላኛው ጨዋታ ፓፎስ ቪያሪያልን 1 ለ 0 አሸንፏል። ዴሪክ ላካሰን የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም