ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መከሩ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መከሩ
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 26/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) እና የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ በሩሲያ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ማክሲም ሬሺትኒኮቭ ከተመራ የሩሲያ ልዑክ ጋር ዛሬ ውይይት አድርገዋል።
ሁለቱ ወገኖች በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ የኢኮኖሚና የፋይናንስ ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተነጋግረዋል።
አገራቱ በትብብር ሊሰሩባቸው በሚችሉ መስኮች ላይም ሀሳቦችን ተለዋውጠዋል።