የኢትዮጵያ ዋንጫ የሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች በህዳር ወር መጀመሪያ ይካሄዳሉ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ዋንጫ የሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች በህዳር ወር መጀመሪያ ይካሄዳሉ
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 26/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ ዋንጫ የሁለተኛ ዙር ደልድል ዛሬ ይፋ አድርጓል።
በዚሁ መሰረት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲዳማ ቡና፣ ድሬዳዋ ከተማ ከሃዋሳ ከተማ፣ መቀሌ 70 እንደርታ ከፋሲል ከነማ፣ ምድረገነት ሽሬ ከመቻል፣ ወላይታ ድቻ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣ አርባምንጭ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከኢትዮጵያ መድን፣ ሀዲያ ሆሳዕና ከነጌሌ አርሲ፣ ባህር ዳር ከተማ ከሸገር ከተማ እና አዳማ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ይጫወታሉ።
ሀላባ ከተማ ከቦዲቲ ከተማ፣ ደብረብርሃን ከተማ ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ፣ ቢሾፍቱ ከተማ ከደሴ ከተማ፣ ሐረር ከተማ ከአቃቂ ክፍለ ከተማ፣ ንብ ከየካ ክፍለ ከተማ እና ቤንችማጂ ቡና ከጋሞ ጨንቻ ሌሎች የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው።
የኢትዮጵያ ዋንጫ የሁለተኛ ዙር መርሃ ግብር ከህዳር 2 እስከ 4 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
ጨዋታዎቹ አዲስ አበባ ስታዲየም፣ ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም፣ ሃዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ እና ጅማ ስታዲየም ይደረጋሉ።
በመጀመሪያው ዙር ውድድር የከፍተኛ ሊግ ክለቦች ብቻ የተሳተፉ ሲሆን አሸናፊ ቡድኖች በሁለተኛው ዙር ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቡድኖች ጋር በመቀላቀል ይጫወታሉ።
ወላይታ ድቻ የወቅቱ የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ነው።
የኢትዮጵያ ዋንጫ የሚያሸንፍ ቡድን በቀጣዩ ዓመት ኢትዮጵያን ወክሎ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ይሳተፋል።