ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ለትምህርት ጥራት ትኩረት በመስጠት ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋን ለማፍራት እየሰራ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ለትምህርት ጥራት ትኩረት በመስጠት ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋን ለማፍራት እየሰራ ነው
ጋምቤላ፤ ጥቅምት 26/2018 (ኢዜአ)፡- የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ለትምህርት ጥራት ትኩረት በመስጠት ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋን ለማፍራት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ድሪባ ኢቲቻ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው ለትምህርት ጥራት ትኩረት በመስጠት የምሩቃን ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መጠነ ማለፍን በሁለት እጥፍ ማሳደጉን ተናግረዋል።
ተግባሩን በትምህርት ዘመኑ ለማጠናከር ለግብዓትና ምድረ ግቢን ለመማር ማስተማር ምቹ በማድረግ ብቁና ተወዳደሪ ዜጋ ለመፍጠር በትጋት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በትምህርት ሚኒስቴርና በዩኒቨርሲቲዎች መካከል በትምህርት ዘመኑ የተፈረመውን የአፈፃፀም ውል ስምምነት ወደ እያንዳንዱ ፈፃሚ በማውረድ የተሳለጠ የመማር ማስተማር፣ የምርምርና የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ስራዎች እንዲከናወኑ እየተደረገ ነው ብለዋል።
በተለይም ካለፈው ዓመት በተሻለ መልኩ የምሩቃን ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መጠነ ማለፍ ከፍ ለማድረግ በተጨማሪ ክፍለ ጊዜ ተማሪዎችን ለማብቃት በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ዶክተር ድሪባ ገልጸዋል።
በትምህርት ዘመኑ የዩኒቨርሲቲውን የመፈጸም አቅም ለማጎልበትና የሚፈለገውን ጥራት ለማምጣት በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ያነሱት ደግሞ በዩኒቨርሲቲው የኢንጅነሪንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ዲን መምህር ዶል ጉኝ ናቸው።
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በዘንድሮው ዓመት አዲስ የተመደቡለትን 500 ተማሪዎች ተቀብሎ ማስተማር መጀመሩ ይታወሳል።