አርሰናል ስላቪያ ፕራግን በማሸነፍ የሻምፒዮንስ ሊጉን የመሪነት ደረጃ ይዟል - ኢዜአ አማርኛ
አርሰናል ስላቪያ ፕራግን በማሸነፍ የሻምፒዮንስ ሊጉን የመሪነት ደረጃ ይዟል
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25/2018(ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ መርሃ ግብር አርሰናል ስላቪያ ፕራግን 3 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በፎርቹና አሬና ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ማይክል ሜሪኖ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ቡካዮ ሳካ ቀሪዋን ጎል በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ ላይ አሳርፏል።
አርሰናል በኳስ ቁጥጥር ብልጫ የወሰደ ሲሆን በርካታ የግብ እድሎችንም ፈጥሯል።
ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል የሻምፒዮንስ ሊግ የሊግ ውድድር ፎርማት ደረጃን በ12 ነጥብ መምራት ጀምሯል።
መድፈኞቹ ባለፉት ስምንት ጨዋታዎች ግብ አልተቆጠረባቸውም።
ተቀይሮ የገባው የአርሰናሉ ማክስ ዳውማን በ15 ዓመት 308 ቀናት በመጫወት በሻምፒዮንስ ሊጉ ታሪክ የተሰለፈ በእድሜ ትንሹ ወጣት ተጫዋች ሆኗል።
በውድድሩ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ስላቪያ ፕራግ በሁለት ነጥብ 30ኛ ደረጃን ይዟል።
በሌላኛው መርሃ ግብር ናፖሊ እና ኢንትራክት ፍራንክፈርት ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።