መቻል ዳግም የሊጉን መሪነት ተረከበ - ኢዜአ አማርኛ
መቻል ዳግም የሊጉን መሪነት ተረከበ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት መቻል ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ መሐመድ አበራ እና ብሩክ ማርቆስ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
በሊጉ ሶስተኛ ድሉን ያሳካው መቻል በ10 ነጥብ የሊጉን መሪነት ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ተረክቧል።
በአንጻሩ በሊጉ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በአንድ ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
ቀን ላይ በተደረጉ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድሬዳዋ ከተማን 2 ለ 0፣ አዳማ ከተማ አርባምንጭ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፈዋል።
ጨዋታዎቹን ተከትሎ የአራተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ተጠናቋል።
የአምስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከጥቅምት 28 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ እንደሚካሄዱ የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል።