ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድል ቀንቶታል 

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይርጋጨፌ ቡናን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል። 

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ እፀገነት ግርማ፣ መሳይ ተመስገን፣ ታሪኳ ዴቢሶ እና ንግስት በቀለ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደረገው ንግድ ባንክ ድል ቀንቶታል። 

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በካፍ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ተሳትፎ ምክንያት የመጀመሪያ ሶስት ሳምንታት ጨዋታዎቹን አላደረገም።

ጨዋታዎቹ በተስተካካይ መርሃ ግብርነት ተይዘዋል። 

አዲስ አዳጊው ይርጋጨፌ ቡና በሊጉ የመጀመሪያ ሽንፈቱን አስተናግዷል። 

ቀን ላይ በተደረገ ጨዋታ መቻል እና ሲዳማ ቡና ሁለት አቻ ተለያይተዋል። 

ጨዋታዎቹን ተከትሎ የአራተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ተጠናቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም