ቀጥታ፡

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አዳማ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ጨዋታዎች በመካሄድ ይገኛሉ።

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድሬዳዋ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።

ዩጋንዳዊው ሳይመን ፒተር እና የድሬዳዋ ከተማ ድልአዲስ ገብሬ በራሱ ግብ ላይ ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን ሲያስመዘግብ ድሬዳዋ ከተማ ሁለተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ሌላኛው መርሃ ግብር አዳማ ከተማ አርባምንጭ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።

ወጣቱ አጥቂ ቢኒያም አይተን በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ ላይ አሳርፏል። 

አዳማ ከተማ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን ሲያገኝ አርባምንጭ ከተማ በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ሽንፈት አስተናግዷል።

አርባምንጭ ከተማ በሊጉ እስከ አሁን ምንም ጨዋታ ማሸነፍ አልቻለም።

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከመቻል ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም