በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መቻል እና ሲዳማ ቡና አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መቻል እና ሲዳማ ቡና አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 25/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት መርሃ ግብር መቻል እና ሲዳማ ቡና ያደረጉት ጨዋታ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቱሪስት ለማ ሁለቱን ግቦች ለመቻል አስቆጥራለች።
ምትኬ ብርሃኑ የሲዳማ ቡናን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፋለች።
ውጤቱን ተከትሎ መቻል በሰባት ነጥብ ሶስተኛ፣ ሲዳማ ቡና በአምስት ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዘዋል።
የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከይርጋጨፌ ቡና ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።