የሰላም ጸር የሆኑ ባንዳዎችን የጥፋት እቅድ በማምከን ለዘላቂ ሰላምና ልማት እንሰራለን- የመንግስት ሰራተኞች - ኢዜአ አማርኛ
የሰላም ጸር የሆኑ ባንዳዎችን የጥፋት እቅድ በማምከን ለዘላቂ ሰላምና ልማት እንሰራለን- የመንግስት ሰራተኞች
ወልዲያ ፤ጥቅምት 25/2018 (ኢዜአ)፦ የልማት አደናቃፊና የሰላም ጸር ባንዳዎችን በማጋለጥና በመታገል ለዘላቂ ሰላምና ልማት እንሰራለን ሲሉ በሰሜን ወሎ ዞን የሚገኙ የመንግስት ሠራተኞች ገለጹ።
"የውጭ ባዳ እና የውስጥ ባንዳዎችን ቅዠት በማምከን አንፀባራቂ ድሎችን እናስመዘግባለን" በሚል መሪ ሃሳብ በሰሜን ወሎ ዞን የሚገኙ የመንግስት ሠራተኞች የውይይት መድረክ አካሂደዋል።
በውይይቱ መድረኩ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎችም የልማት አደናቃፊና የሰላም ጸር የሆኑ ባንዳዎችን በማጋለጥና በመታገል ለዘላቂ ሰላምና ልማት እንሰራለን ሲሉ አረጋግጠዋል።
ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል አቶ ሲሳይ አለሙ እና አቶ አበራ አብርሃ፤ ለኢትዮጵያ መልካም ነገር የማያስቡ እና የማይመኙ ታሪካዊ ጠላቶች በሚያገኙት አጋጣሚ ሁሉ ለጥፋት እየሰሩ መሆኑን አንስተዋል።
በተለይም የውስጥ ባንዳዎችን ተልእኮ ፈፃሚ በማድረግ የልማት ስራዎች እንዲደናቀፉ እና በተለያዩ አካባቢዎች ሰላም እንዲደፈርስ እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በመሆኑም የልማት አደናቃፊና የሰላም ጸር የሆኑ ባንዳዎችን በማጋለጥና በመታገል ጭምር ለዘላቂ ሰላምና ልማት እንሰራለን ሲሉ አረጋግጠዋል።
የሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቱ አሰፋ፤ የባንዳዎችና ባዳዎች የጥፋት ሙከራና እንቅስቃሴ በሰላም ወዳዱ ህብረተሰብ እና በጸጥታ ሃይሉ ጥብቅ ቁጥጥር እየመከነ መሆኑን ገልጸዋል።
በቀጣይም ሰላምን ለማጽናትና ልማትን ለማስቀጠል በሚደረገው ጥረት የህዝቡ በተለይም የመንግስት ሰራተኛው እገዛና ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።