በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና አዳማ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና አዳማ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል
           አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ተደርገዋል።
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ድሬዳዋ ከተማን 3 ለ 0 አሸንፏል። ዳግማዊት ሰለሞን ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርታለች።
                
                
  
በሌላኛው ጨዋታ አዳማ ከተማ በነፃነት መና ግብ አርባምንጭ ከተማን 1 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል።
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከታንዛንያ ጋር በነበረው የአፍሪካ ዋንጫ የመጨረሻ ዙር ማጣሪያ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የሊጉ ውድድር ትናንት መጀመሩ ይታወቃል።
ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች ሃዋሳ ከተማ አዲስ አበባ ከተማን እና ሸገር ከተማ ባህር ዳር ከተማን በተመሳሳይ 2 ለ 0 ሲያሸንፉ ቦሌ ክፍለ ከተማ ከልደታ ክፍለ ከተማ ሁለት አቻ ተለያይተዋል።
የአራተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ነገ ይጠናቀቃል።