በፕሪሚየር ሊጉ ሸገር ከተማ እና ሃዋሳ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል - ኢዜአ አማርኛ
በፕሪሚየር ሊጉ ሸገር ከተማ እና ሃዋሳ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ተካሄደዋል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ አዲስ አዳጊው ሸገር ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን በያሬድ መኮንን ግብ 1 ለ 0 አሸንፏል።
ውጤቱን ተከትሎ ሸገር ከተማ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን ሲያስመዘግብ ቅዱስ ጊዮርጊስ በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ሽንፈቱን አስተናግዷል።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው ጨዋታ ሃዋሳ ከተማ መቀሌ 70 እንደርታን 3 ለ 1 ረቷል።
ጌታነህ ከበደ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ያሬድ ብሩክ ቀሪዋን ጎል ለሃዋሳ ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ሱሌይማን ሃሚድ ለመቀሌ 70 እንደርታ ብቸኛዋን ጎል ከመረብ ጋር አገናኝቷል።
ሃዋሳ ከተማ በሊጉ ሶስተኛ ድሉን ሲያስመዘግብ በተቃራኒው መቀሌ 70 እንደርታ ሶስተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።
ዛሬ አስቀድሞ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን ሀዲያ ሆሳዕናን 2 ለ 1 አሸንፏል።