ቀጥታ፡

የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ድሉን አስመዘገበ 

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን ሀዲያ ሆሳዕናን 2 ለ 1 አሸንፏል። 

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ዩጋንዳዊው አለን ካይዋ እና የሀዲያ ሆሳዕናው ተከላካይ ዳግም ንጉሴ በራሱ ግብ ላይ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። 


 

ተመስገን ብርሃኑ ለሀዲያ ሆሳዕና ብቸኛውን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል። 

ውጤቱን ተከትሎ የሊጉ የወቅቱ የዋንጫ ባለቤት ኢትዮጵያ መድን በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ሶስት ነጥብ አግኝቷል። መድን ሁለት ተስተካካይ ጨዋታ ይቀረዋል። 

ሀዲያ ሆሳዕና በሊጉ ሁለተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል። ቡድኑ በውድድር ዓመቱ እስከ አሁን ድል ማስመዝገብ አልቻለም።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም