ቀጥታ፡

ማንችስተር ሲቲ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ ያደረገበትን ወሳኝ ድል አስመዘገበ 

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ማንችስተር ሲቲ ቦርንማውዝን 3 ለ 1 አሸንፏል።

ማምሻውን በኢትሃድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አርሊንግ ሃላንድ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ኒኮ ኦራይሊ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ጋር አገናኝቷል።

ሃላንድ በሊጉ ያስቆጠራቸውን ግቦች ወደ 11 ከፍ በማድረግ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት መሪነቱን አጠናክሯል።

ታይለር አዳምስ ለቦርንማውዝ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ማንችስተር ሲቲ በሊጉ ስድስተኛ ድሉን በማስመዝገብ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል።

በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቦርንማውዝ በ18 ነጥብ ከሶስተኛ ደረጃ ወደ አራተኛ ዝቅ ብሏል።

ቀን ላይ በተደረገ ጨዋታ ዌስትሃም ዩናይትድ ኒውካስትል ዩናይትድን 3 ለ 1 በመርታት ከሶስት ተከታታይ ሽንፈት በኋላ ወደ ድል ተመልሷል።  በሊጉም ሁለተኛ ድሉን አግኝቷል።

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ነገ ሰንደርላንድ ከኤቨርተን በሚያደርጉት ጨዋታ ይጠናቀቃል።

ሊጉን አርሰናል በ25 ነጥብ እየመራ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም