በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት ጨዋታ ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት ጨዋታ ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 23/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት መረሃ ግብር ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻን 2 ለ 0 አሸነፈ።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ከ9 ሰዓት ጀምሮ በተደረገው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የሲዳማ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች ፍቅረ እየሱስ ተክለብርሃን በ9ኛው እና መላኩ አሰፋ በ90ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥረዋል።
በተመሳሳይ በሊጉ አራተኛ ሳምንት ጨዋታ 10 ሰዓት ላይ የተጀመረው የነጌሌ አርሲ እና ባህር ዳር ከተማ ፍልሚያ በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተከናወነ ሲሆን በሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ እስካሁን ጎል አልተስተናገደም።
ወላይታ ድቻ በሊጉ እስካሁን ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻው 20ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
እንዲሁም ፋሲል ከነማ ከምድረ ገነት ሽሬ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት መርሃ ግብር እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።