ኢትዮ ኤሌክትሪክ ዳግም የሊጉን መሪነት ተረክቧል - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ዳግም የሊጉን መሪነት ተረክቧል
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ኢትዮጵያ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሀብታሙ ሸዋለም በ48ኛው ደቂቃ ላይ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ድሉን ያስመዘገበው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ10 ነጥብ የሊጉን መሪነት ከመቻል ተረክቧል።
በሊጉ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና በአራት ነጥብ 10ኛ ደረጃን ላይ ይገኛል።