ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳል

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 23/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ውሎ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ። 

ኢትዮጵያ ቡና ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ከቀኑ 7 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም ይጫወታሉ። 

ቡናማዎቹ በሊጉ እስከ አሁን ባደረጓቸው ሶስት ጨዋታዎች አንድ ጊዜ ሲያሸንፉ በተመሳሳይ አንድ ጊዜ ሽንፈት ገጥሟቸዋል። አንድ ጊዜ ነጥብ ተጋርቷል። ቡድኑ በአራት ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ተጋጣሚው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ካደረጋቸው ሶስት ጨዋታዎች ሁለቱን ሲያሸንፍ አንድ ጊዜ አቻ ወጥቷል። በሰባት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። 


 

ከቀኑ 10 ሰዓት ነጌሌ አርሲ ከባህር ዳር ከተማ በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ነገሌ አርሲ በአንድ ነጥብ 18ኛ፣ ባህር ዳር ከተማ በአምስት ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

ሁለቱ ቡድኖች በፕሪሚየር ሊጉ ሲገናኙ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። 

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ሲዳማ ቡና ከወላይታ ድቻ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። 

ሲዳማ ቡና በስድስት ነጥብ አራተኛ ደረጃን ሲይዝ ወላይታ ድቻ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻው 20ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ጨዋታው ሲዳማ ቡና በሶስተኛ ሳምንት በፋሲል ከነማ ካጋጠመው ሽንፈት ለማገገም በአንጻሩ ወላይታ ድቻ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን ለማስመዝገብ የሚያደርጉት ነው። 

ፋሲል ከነማ ከምድረ ገነት ሽሬ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ።

ከሶስት ጨዋታዎች ሰባት ነጥብ ያገኘው ፋሲል ከነማ በሰባት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ምድረ ገነት ሽሬ በአምስት ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት መርሃ ግብር እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም