የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጨማሪ Airbus A350-900 አውሮፕላን ተረከበ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጨማሪ Airbus A350-900 አውሮፕላን ተረከበ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 22/2018(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ እጅግ ቅንጡ የሆነውንና በዚህኛው ሞዴል 21ኛውን Airbus A350-900 (ET-BCE) አውሮፕላን ተረክቧል።
አየር መንገዱ ዛሬ ማለዳ የተረከበው ይህ አውሮፕላን፤ 340 ሰው የመጫን ዐቅም እንዳለውም አየር መንገዱ ለኢዜአ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህን አውሮፕላን መረከቡ በዓለም አቀፍ በዘርፉ ያለውን ምቹ አገልግሎት አሰጣጥ በይበልጥ እንደሚያሳድገው ተጠቁሟል።