ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በመስከረም እናጥቅምት ወር 2018 ዓ.ም ያከናወኗቸው ዋና ዋና ተግባራት - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በመስከረም እናጥቅምት ወር 2018 ዓ.ም ያከናወኗቸው ዋና ዋና ተግባራት
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በመስከረም እናጥቅምት ወር 2018 ዓ.ም በመሠረተ ልማት፣ በገጠር ልማት፣ በአስተዳደራዊ ማሻሻያ እና በዲፕሎማሲያዊ ትብብር ላይ ያተኮሩ ተከታታይ አገራዊ እና ዓለም አቀፍ ተግባራትን አካናውነዋል።
ያለፈውን ወር ተግበራት በጨረፍታ እነሆ፥
የከተማ ልማት እና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በተመለከተ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ከዳንጎቴ ግሩፕ ጋር በመተባበር ለሚገነባው የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ እና በጎልደን ኮንኮርድ ግሩፕ አማካኝነት ለሚገነባው የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ መሠረት መጣላቸው ከካናወኗቸው ቀዳሚ ተግባራት የሚጠቀሱ ናቸው። የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ከሂላል የነዳጅ ስፍራ ድፍድፍ ነዳጅ በማውጣት፣ በማጣራትና በማጠራቀም በአመት 3.5 ሚሊዮን ቶን የማምረት አቅም አለው።
በሌላ በኩልም የማዳበሪያ ፋብሪካው ከካሉብ የጋዝ ስፍራ በማውጣት እና 108 ኪሎሜትር የማጓጓዣ ቱቦ በመጠቀም በአመት 3 ሚሊዮን ቶን አምርቶ ያቀርባል። ይህ ፕሮጀክት የኢትዮጵያ በአፈር ማዳበሪያ ራስን የመቻል ውጥኗን ለማሳካት እና የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ የምትከተለው ቁልፍ ስትራቴጂ ነው።
በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሶማሌ ክልል ካሉብ በአመት 111 ሚሊዮን ሊትር ማምረት የሚችለውን የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር መርቀዋል። በተመሳሳይ በአመት 1.33 ቢሊዮን ሊትር የማምረት አቅም የሚኖረውን ሁለተኛውን ዙር ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስጀመረዋል። ይህ ፕሮጀክት ከፈሳሽ ተፈጥሮ ጋዝ ምርት ባሻገር በኃይል ማመንጫ ዘርፉም 1000 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም በመያዝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
ፕሮጄክቱ ጋዝ ከማምረት ባሻገር፤ ለማዳበሪያ ማምረቻ ወሳኝ የሆነውን ግብዓት በማቅረብ ሀገሪቱ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ለምታደርገው ጥረት የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ ያገለግላል። እንዲሁም ይህ ፕሮጀክት ለኃይል ማመንጫ እና የክሪፕቶ-ማይኒንግ ሥራዎቻችን አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን የሚያቀርብ ይሆናል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በዚያው ሶማሌ ክልል ጂጂጋ ከተማ በነበራቸው ጉብኝት፤ ከጥር ወር 2017 ዓ.ም የመጨረሻ ጉብኝታቸው ወዲህ የተመዘገበውን የከተማዋን ፈጣን ለውጥ ተመልክተዋል። በመላው ከተማዋ በሺዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ መኖሪያ ቤቶች እየተገነቡ ሲሆን፥ በኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች በሁሉም አካባቢ የመኖሪያ ሁኔታን በግልጽ እያሻሻሉ ይታያሉ።
ወደ መጠናቀቂያ ምዕራፍ የደረሰው የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ለምስራቁ የሀገሪቱ ክፍል አዲስ ዋጋ የጨመረ እድል እየፈጠረ ስለመሆኑም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአድናቆት ገልጸዋል። በዚህ መንፈስ የሶማሌ ክልል በቱሪዝም አዳዲስ እድሎችን እየከፈተ ይገኛልም ብለዋል።
በዚሁ ወር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ጋር በመሆን አሁን ላይ የተጠናቀቀውን የሳር ቤት-ጀርመን አደባባይ-ጋርመንት እና ፉሪ አካባቢ የኮሪደር ልማት ሥራ ጎብኝተዋል። 589 ሄክታር በላይ የሚሸፍነው ከባቢ ከካዛንቺስ ቀጥሎ ሰፊው የልማት ስፍራ ሆኗል። ፕሮጀክቱ 16.5 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ፣ የ3 ኪሎ ሜትር ተጨማሪ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ብሎም 33 ኪሎ ሜትር የተዘረጋ የእግረኛ መንገድ አካትቷል። የፕላዛዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ የሕፃናት መጫወቻዎች እና 5.2 ኪሎ ሜትር የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራ ተከናውኗል።
የመኪና ማቆሚያዎች፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ኃይል መሙያ ስፍራዎች፣ በግል እና የመንግሥት ተቋማት የተገቡ 1107 ሱቆች በልማት ሥራው የተሠሩ ናቸው። ይህ ተግባር ዘመናዊ፣ ለኑሮ ምቹ እና በኢኮኖሚ የበለፀጉ ከተሞችን እውን የማድረግ ሰፊ ሀገራዊ ራዕይ አካል ነው።
የገጠር ትራንስፎርሜሽን እና የግብርና መዘመን
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የመንግስታቸውን የገጠር ልማት አጀንዳ እውን ለማደረግ ባከናወኑት ቁልፍ ተግባር፤ በክረምት በጎፈቃድ መርሃግብር በሀላባ ፣ ከምባታ ፣ ሀድያ እና ስልጤ ዞኖች የተገነቡ ሞዴል የገጠር መንደሮችን አሰረክበዋል። እነዚህ መንደሮች የአርሶ አደሮችን እና አርብቶ አደሮችን ሕይወትለማሻሻል ለሚደረገው ጥረት ተስፋ ሰጪ መሳያዎች ናቸው።
ቤቶቹ የፀሃይ ኃይል ማመንጫ የተገጠመላቸው፣ ለማብሰል ደግሞ ከእንስሳት እዳሪ ባዮጋዝ የሚጠቀሙ፣ የተለየ ሳሎን፣መጸዳጃ እና ሰርቪስ ቤቶች የተሟላላቸው ናቸው።
ንጽህናንበሚያረጋግጥ እና የአኗኗር ደረጃን ከፍ በሚያደርግ አኳኋን የተለየየእንስሳት በረት ተሰርቶላቸዋል።
እነዚህ ሞዴል መንደሮች ኢትዮጵያ የገጠር አኗኗርን ለማሻሻል አዲስ ምዕራፍ መክፈቷን ያመለክታሉ። በተጨማሪም እነዚህ የገጠር ኮሪደር ልማት መንደሮች የገጠሩን አኗኗር ለማሳደገ የሀገራዊ ሕልም አካል በመሆን ተስፋፍተው የሚሰሩ አንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናግረዋል።
ወደ ፊትም የየአካባቢ አመራሮች ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተሠሩትን ሞዴል መንደሮች በመጪው አመት በየዞኑ ወደ100 ቤቶች እንዲያሳድጉ አሳስበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በምስራቅ ሸዋ ዞን በነበራቸው ጉብኝት በክረምት የስንዴ ምርት ሥራዎች የተገኘውን ውጤት የምርት አሰባሰቡን በመመልከት የገመገሙ ሲሆን፤ የበጋ ስንዴ ሥራን በወቅቱ አስጀምረዋል። በዚያው አካባቢ የሙዝ፣ ፓፓያ እና አሳ ክለስተር ሥራዎችንም ተመልክተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በባሌ ዞን፣ ደሎ መና ወረዳ በመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር አማካኝነት የተጀመረውን የወልመል ወንዝ መስኖ ልማት ፕሮጀክትን መርቀዋል። ፕሮጀክቱ ዘላቂ የገጸምድር የመስኖ ሥርዓት በመገንባት የግብርና ስራው ለዘመናት በዝናብ ውሃ ላይ ተመስርቶ የነበረውን የአካባቢውን ሕዝብ ዘላቂ የኑሮ ዘዴ ለማጎናፀፍ ታልሞ ተከናውኗል።
ፕሮጀክቱ በሙሉ አቅሙ ወደ ተግባር በሚገባበት ወቅት 20,000 ለሚሆኑ አርሶአደሮች ለሚያገለግል 9687.45 ሄክታር የእርሻ መሬት አስተማማኝ የመስኖ አቅርቦት ይኖረዋል።
የኢኮኖሚ አስተዳደር እና የማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸም ግምገማ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የ2018 ዓመተ ምህረት የመጀመሪያ 100 ቀናት የማክሮኢኮኖሚ አፈፃፀም ግምገማ በኮይሻ ግድብ ከሚኒስትሮች ምክር ቤት ጋር ውይይት አድረገዋል።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የመቶ ቀን እቅድ ግምገማ የአለምን የኢኮኖሚ አዝማሚያ፣ የኢትዮጵያን ማክሮኢኮኖሚ የመጀመሪያ ሩብ አመት አፈፃፀም እንዲሁም የእድገት አዝማሚያን እና አጠቃላይ ምልከታን ያካተተ አቅርቦትን አካትቷል። በአለም የኢኮኖሚ ልማት አውድ ሲታይ ኢትዮጵያ ልዩ ጥንካሬ እና የእድገት ፍጥነት አሳይታለች። በ2017 የበጀት አመት የኢትዮጵያ አጠቃላይ የኢኮኖሚ አፈፃፀም በጥንካሬው በመቀጠል 9.2 በመቶ አመታዊ የGDP እድገት እስመዝግቧል።
የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለፍትህ መዘመን
ቴክኖሎጂ መር አዘማኝነት ላይ የሚያተኩረው የዲጂታል 2025 ስትራቴጂ በስኬት መጠናቀቅን ተከትሎ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በበለጠ የማሽን ግብዓት (አቶሜሽን) በመጠቀም አገልግሎት አሰጣጥን ለማጠናከር ዲጂታል 2030ን ለማስጀመር እየተሰራ መሆኑን አሳውቀዋል።
የፍትኅ ተደራሽነት ለዜጎች እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ መሆኑን እውቅና በመሥጠትም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፈጣን፣ ግልጽ እና ውጤታማ የሆነ ሥርዓት ለመገንባት በጽናት እየሠራ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደቶች በአግባቡ መቀዳታቸውን ለማረጋገጥ ድምጽን ወደ ጽሁፍ የሚቀይር ብሎም በአስተማማኝ ሁኔታ ተጠብቀው የሚቆዩበትን ስማርት የፍርድ ሥርዓት አልምታል። ሥርዓቱ ፍትኅ ፈላጊዎች ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው በአካል በችሎት መገኘት ሳይጠበቅባቸው ካሉበት ሆነው ጉዳያቸውን ለመከታተል ያስችላቸዋል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። በአሁኑ ወቅት 24 የፌደራል ቅርንጫፎች በሥርዓቱ የተሸፈኑ መሆኑ አበረታች ሲሆን በቅርቡ ወደ ክልሎችም እንደሚስፋፋ ይጠበቃል።
በሚዲያ፣ በባህል እና በቱሪዝም ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራት
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) Pulse of Africa የተሰኘ የፓን አፍሪካ ሚዲያ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተዋል። ሚዲያው ጠቅላይ ሚኒስትር እኤአ በ2022 በ35ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የአፍሪካን እይታ እና ትርክት የሚያንፀባርቅ የአኅጉራዊ ሚዲያን አስፈላጊነት አስመልክተው ያቀረቡትን ጥሪ በመመርኮዝ የተመሠረተ ነው።
Pulse of Africa የአፍሪካን ድምፆች የሚያጎላ፣ ቀጠናዊ ትስስርን የሚያጠናክር እና አኅጉራዊ ስኬቶችን፣ ተግዳሮቶችን እና ሕልሞችን በአፍሪካዊ እይታ የሚገልጥ ሚዲያ የመሆን አላማ አለው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት፥ የPulse of Africa ሚዲያ ሥራ መጀመር አፍሪካን በአሉታዊ ገጽታ የማቅረብ ሥራን ለመመከት ብሎም የራሳችንን ትርክት በራሳችን የመቅረጽ ተግባራችንን የምናፀናበት ጠቃሚ ርምጃ ነው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማይት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከተለያዩ የቀድሞ እና በሥራ ላይ ካሉ የመንግሥት ኃላፊዎች ጋር በመሆን፥ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ምስራቅ 400ኪሎ ሜትሮች ርቀት በኦሮምያ ክልል ባሌ ዞን የሚገኘውን እና ከ2000 ኪሎሜትር ስኬር በላይ ስፋት በሚሸፍነው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ተገኝተው መልከታ አድርገዋል። በዚህም በአካባቢው በመገንባት ላይ ያለውን የዲንሾ ሎጅ እና በአቅራቢያው በመገንባት ላይ ያለውና በቅርቡ የሚጠናቀቀው የሶፍኡመር ሎጅ ቱሪዝም ፕሮጀክት ጎብኝተዋል።
ሁለቱም ፕሮጀክቶች ቱሪዝምን ለኢኮኖሚያዊ ለውጥ እንደ ቁልፍ አነቃቂ ዘርፍ በማስቀመጥ የኢትዮጵያን የአስር ዓመት ስትራቴጂካዊ እቅድ ለማሳለጥ የተነደፉ ናቸው። በተለይም የሶፍ ኦመር የዋሻ ልማት ፕሮጀክት በሀገሪቱ ውስጥ ካሉት እጅግ ድንቅ የተፈጥሮ ምልክቶች አንዱ በመሆኑ፣ ለጎብኚዎች የተሻለ እና ተደራሽ የሆነ አገልግሎት ያሟላል።
በመንገድ መሠረተ ልማት ረገድ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና አብሯቸው የተጓዘው ልኡካን ቡድን የሮቤ-ጎሮ-ሶፍኡመር-ጊኒር መንገድ የማሻሻያ ፕሮጀክትን ተመልክተዋል። ይህ መንገድ ከፍተኛ አምራች የሆኑትን የምሥራቅ ባሌ እና የባሌ ዞኖችን ምርታቸውን ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ የሚያገናኝ ነው። ይኽ መሥመር ተደራሽነትን እና የኢኮኖሚ ተያያዥነትን ብቻ ሳይሆን እንደ ሶፍኡመር ዋሻ እና የባሌ ተራሮች ወደ መሰሉት ዐበይት የመስኅብ ሥፍራዎች ጉዞን የሚያሳልጥ ነው።
በዚሁ ጉብኝት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የወይብ ወንዝ የጎርፍ መቆጣጠሪያ ፕሮጀክትን በተጨማሪነት ተመልክትዋል። ፕሮጀክቱ በሶፍኡመር ዋሻ የሚጓዘውን የወንዙን የውሃ ፍሰት በመቆጣጠር አመቱን ሙሉ ወደ ዋሻው የሚደረግ ጉዞ እንዳይስተጓጎል ለማድረግ ብሎም የዋሻውን ሥነምኅዳር ለመጠበቅ ታልሞ የተሠራ ነው። ሁሉም ሥራዎች ቀጣይነት ላለው ልማት መንግስት ያለው ጽኑ አቋም እና ተግባር የሚገልጡ እንደሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
በመጨረሻ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በባሌ ዞን ከተለያዩ አመራሮች ጋር ያደረጉት ጉብኝት መዳረሻ አስደማሚው የፊንጫ ሀበራ ፏፏቴ ሆኗል። ይህ ፏፏቴው ወደ ሶፍኡመር የዋሻ ሥርዓት የሚደመረውን የወይብ ወንዝ የሚቀላቀል ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ቀይ ቀበሮ የሚገኝበት፣ የድንቅ የአዕዋፍ መገኛና በቅርቡ የዋሻ መስህብ የተገኘበት እንዲሁም የራፉ ውብ የዐለት ደን አቅራብያ የሚገኝ ነው። በቅርቡ በአካባቢው የሚገነባው ማረፊያ ሲጠናቀቅም ለጎብኝዎች የበለጠ ሳቢ እና ምቹ ይሆናል።
የፓርላማ ተሳትፎ እና ብሔራዊ ውይይት
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ካከናወኗቸው ቁልፍ ተግባራት ውስጥ አንዱ፥ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 5ኛ ዓመት፣ 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ምላሽና ማብራሪያ በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው።
በዚህ መሠረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በኢኮኖሚው ዘርፍ የተገኘውን ውጤት ሲያብራሩ፤ ኢትዮጵያ ከግብርና መር ኢኮኖሚ ወደ ብዝሃ ዘርፍ ማለተም ወደ ኢንዱስትሪ እና አገልግሎት ዕድገት መሸጋገሯ አስደናቂ ውጤቶችን እንዳስገኘ ጠቅሰዋል። ይህም ፈጣን የግብርና ልማት መስፋፋት እውን አንዲሁን፤ ከፍተኛ የወጪ ንግድ ገቢ እና የውጭ ምንዛሬ ክምችት እንዲመጨመር ማስቻሉን ጠቅሷል።
በአረንጓዴ ልማት ውጥኖች፣ በትራንስፖርት መሠረተ ልማት እና በኋይል ማመንጫፕሮጀክቶች ላይ የተተገበሩ ዋና ዋና የኢንቨስትመንት ሥራዎች ምርታማነትን እና ዘላቂ ልማትን እያመጡ ሲሆን፤ ጥንቃቄ የተሞላበት የዕዳ አስተዳደር እና የታለሙ የደጎማ አርምጃዎች ደግሞ የዋጋ ግሽበትን አረጋጋተዋል።
መንግስት የተቋማዊ አቅምን በማጠናከር፣ ዲጂታላይዜሽን ሥራን በማስፋፋት፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶችን በኮዲንግ(coding) በማሰልጠን እና በመላ አገሪቱ የአንድ መስኮት ማዕከል የአገልግሎት አሰጣጥንበማዘመን ላይ ትኩረት ማድረጉን አፅንዖት ሰጥተዋል።
ሰላምና ጸጥታን በሚመለከት ጠቀላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሲናገሩ፤ ኢትዮጵያ ለቀጠናዊ መረጋጋት፣ ለንግግር እና ለብሔራዊ አንድነት ቁርጠኝነት አንደሆነች አረጋግጠዋል። ሀገሪቱን ለማተራመስ የሚጥሩ ውስጣዊም ሆነ ውጫዊ ተዋናዮችን በዚሁ ወቅት አስጠንቅቀዋል። ለኢትዮጵያ ብቸኛው ተመራጭ መንገድ ሰላማዊ የፖለቲካ ሽግግር እና ዴሞክራሲያዊ ውህደት መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል።
መጪውን ብሔራዊ ምርጫ በተመለከተ ደግሞ ሲያብራሩ፣ መንግስት ሁሉን አቀፍ ሂደትን ለማረጋገጥ ዝግጁ መሆኑን ለምክር ቤቱ አረጋግጠዋል። ዲፕሎማሲያዊ እና የውጭ ግንኙነትን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒሰትሩ፤ ኢትዮጵያ የአባይን ውሃ በፍትሃዊ የመጠቀም መብት እንዳላት አስረግጠው ተናግረዋል። ስለሆነም ከጎረቤት ሀገራት ጋር የትብብር ግንኙነት እንዲጠናከር ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።
የቀይ ባህር ጉዳይን በተመለከተ ጥያቄ የተነሳላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ህጋዊ፣ ታሪካዊ፣ መልከዓ ምድራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ ነው ብለን እናምናለን ሲሉ ተደምጠዋል። ኢትዮጵያ ተዘግቶባት መኖር አትችልም ያሉት ጠቅላይ ሚኒሰትሩ፤ ለጎረቤቶቻችን መናገር የምንፈልገው ኢትዮጵያ ስታደግ ለቀጣናውም ልማት ምንጭ ትሆናለች ብለዋል። ስለሆነምየምንፈልገው በትብብር ማደግ ነው ብለዋል።
ዲፕሎማሲያዊ ተሳትፎ እና ቀጠናዊ ትብብርን በተመለከተ
በዲፕሎማሲው መስክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የልዑካን ቡድናቸው በ24ኛው የCOMESA የመሪዎች ጉባኤ በናይሮቢ፣ ኬንያ ተሳትፈዋል። “ዲጂታላይዜሽንን ለቀጠናዊ የእሴት ሰንሰለት መጎልበት በመጠቀም ለዘላቂ እና አካታች እድገት ማዋል” በሚል ጭብጥ በተካሄደው በዚሁ ጉባኤ ላይ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የአፍሪካን የኢኮኖሚ ታሪክ የመቀየር ልዩ እድል እንዳቀረበ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አፅንኦት ሰጥተው አንስተዋል።
እንደ አሕጉር የየሀገራቱን ጥረቶች ለማጣመር እና ቀጠናዊ ትስስሮችን ለማፋጠን ክሂሎቱ እና መሠረቱ እንዳለም ጠቁመዋል። በኢትዮጵያ ዲጂታል ክህሎትን ለማበልጸግ እና አስፈላጊ መሠረተ ልማት ለመገንባት ጥሩ ርምጃዎች ተራምደናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናግረዋል። የጋራ ዲጂታል ነገን ለማሳደግ በትብብር ለመሥራት ኢትዮጵያ ዝግጁ መሆኗንም በዚሁ ጉባኤ ላይ አረጋግጠዋል።
በተመሳሳይ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሳይፕረሱን ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኮንስታንቲኖስ ኮምቦስ ጋር ሁለቱ ሀገራት የዲፕሎማቲክ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ብሎም ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ትብብሮችን ለማጎልበትበሚሰሩበት ጉዳይ ለይ ተወያየተዋል።
የግብር ከፋዮች እውቅና እና የአስተዳደራዊ ማሻሻያ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የ7ኛው የታማኝ ግብርከፋይ እውቅና ሥነሥርዓት ተሸላሚዎችን ያመሰገኑ ሲሆን፣ ለኢትዮጵያ ልማት እና ብልጽግና ጉዞ ለሚያደርጉት አስተዋጽኦ አድንቀዋል። ባለፈው ዓመት ያወጡት ግብር ለጋራ እድገት እና ለሕዝባዊ ጠቀሜታ በሚውሉ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ እንደሚውል ቃልገብተን ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ዛሬ በከተማ ኮሪደሮች የሚታየው ለውጥ ለዚያ ቃል ሕያው ምስክር ሆኖ ይታያል ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለው አንደገለጹት የዛሬ ጥረታችሁ የነገን ትውልድ የተሻለ መፃኢ እድል እየቀረፀ ነው ብለዋል።
ሙስናን እና ሌብነትን ለማስወገድ በምናደርገው ጥረት ሥርዓቶቻችንን ማጠናከራችንን እንቀጥላለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ግብር ከፋዮችም በመሰል ጎጂ ተግባር የተሠማሩ ሰዎችን ባለመተባበር እንዲያግዙ አሳስበዋል። ሰለሆነም በጋራ ግልጽ፣ ተጠያቂነት የሰፈነባት እና የበለጸገች ሀገርመገንባት አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
በጥቅሉ በመስከረም እና በጥቅምት ወር 2018 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢንዱስትሪ፣ በግብርና፣በከተማ ልማት፣ በፍትህ እና በዲፕሎማሲ ዘርፍ የሰጡት ወሳኝ አመራር ኢትዮጵያ ለአካታች ልማት እና ለአገር አቀፍ እድገትያላትን የማይናወጥ ቁርጠኝነት ያረጋገጠ ነው።