ቀጥታ፡

በሊጉ ድሬዳዋ ከተማ ሲያሸንፍ  አዳማ ከተማ ከሀዲያ ሆሳዕና አቻ ተለያይተዋል 

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 20/2018 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ተካሄደዋል።

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ መቀሌ 70 እንደርታን 2 ለ 1 አሸንፏል።

አሰጋኸኝ ጴጥሮስ በ31ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ግብ መቀሌ 70 እንደርታ መሪ ሆኗል።

መሐመድ ኑር ናስር በ49ኛው እና አቤል አሰበ በ93ኛው ደቂቃ  ከመረብ ላይ ያሳረፏቸው ጎሎች ድሬዳዋ ከተማን አሸናፊ አድርገዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ድሬዳዋ ከተማ በስድስት ነጥብ ደረጃውን ወደ ሰባተኛ ከፍ አድርጓል።  መቀሌ 70 እንደርታ በአንድ ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዟል።


 

በተያያዘም አዳማ ከተማ ከሀዲያ ሆሳዕና   በአዲስ አበባ ስታዲየም ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

አዳማ ከተማ በሶስት ነጥብ 11ኛ፣ ሀዲያ ሆሳዕና በሁለት ነጥብ  በግብ ክፍያ ተበልጦ 14ኛ ደረጃን ይዟል።

ጨዋታዎቹን ተከትሎ የሶስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ተጠናቋል።

የአራተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ከጥቅምት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም