ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ መድን ከግብጹ ፒራሚድስ ጋር ዛሬ የመልስ ጨዋታውን ያደርጋል 

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 20/2018 (ኢዜአ):- ኢትዮጵያ መድን በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ሁለተኛ ዙር የመልስ ጨዋታውን ዛሬ ከወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ፒራሚድስ ጋር ያከናውናል። 

የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ካይሮ በሚገኘው ጁን 30 ኤር ዲፌንስ ስታዲየም ይካሄዳል።


 

ክለቦቹ ጥቅምት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ባደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

ብሩክ ሙሉጌታ ለኢትዮጵያ መድን፣ ፊስተን ማዬሌ ለፒራማድስ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። 

ኢትዮጵያ መድን በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈ የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ድልድልን ይቀላቀላል።

መድን በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ሲሳተፍ የዘንድሮው የመጀመሪያው ነው።

ቡድኑ አምናው በታሪኩ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ለመጀመሪያ ጊዜ በማሸነፍ በአህጉራዊ ውድድሩ የሚያሳትፈውን እድል እንዲያገኝ አስችሎታል።


 

የግብጹ ፒራሚድስ ክለብ የወቅቱ የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የዋንጫ ባለቤት ነው። ክለቡ የካፍ አሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫንም አንስቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም