የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሶስተኛ ሳምንት ዛሬ ይጠናቀቃል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሶስተኛ ሳምንት ዛሬ ይጠናቀቃል
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 20/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ውሎ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
አዳማ ከተማ ከሀዲያ ሆሳዕና ከቀኑ 9 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በሊጉ ባደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች ሁለት ነጥብ ብቻ ያገኘው አዳማ ከተማ በሁለት ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል።
ተጋጣሚው ሀዲያ ሆሳዕና በአንድ ነጥብ 18ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ሁለቱ ቡድኖች በ2017 ዓ.ም በሊጉ ባደረጓቸው የእርስ በእርስ ጨዋታዎች በተመሳሳይ አንድ አንድ ጊዜ አሸንፈዋል።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ድሬዳዋ ከተማ ከመቀሌ 70 እንደርታ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ድሬዳዋ ከተማ በሶስት ነጥብ 10ኛ፣ መቀሌ 70 እንደርታ በአንድ ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ጨዋታው ድሬዳዋ ከተማ ተከታታይ ድሉን ለማግኘት፣ መቀሌ 70 እንደርታ በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ድሉን ለማስመዝገብ ይጫወታሉ።
ቡድኖቹ በ2017 ዓ.ም በሊጉ በነበራቸው የእርስ በእርስ ግንኙነት መቀሌ 70 እንደርታ አንድ ጊዜ ሲያሸንፍ በቀሪው ጨዋታ አቻ ተለያይተዋል።