ቀጥታ፡

አርሰናል፣ ቼልሲ፣ ማንችስተር ሲቲ፣ ክሪስታል ፓላስ እና ኒውካስትል ዩናይትድ በካራባኦ ዋንጫ ለሩብ ፍጻሜ አለፉ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 20/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ አራተኛ ዙር  ዛሬ ማምሻውን አምስት ጨዋታዎች ተካሄደዋል።

በኤምሬትስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አርሰናል በቡካዮ ሳካ እና ኢታን ንዋኔሪ ግቦች ብራይተንን 2 ለ 0 አሸንፏል።

ቼልሲ ከሜዳው ውጪ ዎልቭስን 4 ለ 3 አሸንፏል።

አንድሬይ ሳንቶስ፣ ታይሪክ ጆርጅ፣ እስቴቫኦ እና ጂሚ ጊትንስ ግቦቹን ለሰማያዊዎቹ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ለዎልቭስ ዴቪድ ሞለር ዎልፍ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ቶሉ አሮክዳሬ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

የቼልሲው ሊያም ዴላፕ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

ማንችስተር ሲቲ ስዋንሲ ሲቲን በዠርሚ ዶኩ፣ ኦማር ማርሙሽ እና ራያን ቸርኪ ግቦች 3 ለ 1 አሸንፏል። ጎንካሎ ፍራንኮ ለስዋንሲ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ሊቨርፑል በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም በክሪስታል ፓላስ 3 ለ 0 ተሸንፏል። ኢስማይላ ሳር ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር የረሚ ፒኖ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

የሊቨርፑሉ አማራ ናሎ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።

10 ጊዜ ዋንጫውን በማንሳት ስኬታማው ክለብ የሆነው ሊቨርፑል ከውድድሩ ተሰናብቷል።

ቀያዮቹ ካለፉት ስድስት ጨዋታዎች በአምስቱ በመሸነፍ አስቸጋሪ ጊዜ በማሳለፍ ላይ ይገኛሉ።

የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ኒውካስትል ዩናይትድ ቶተንሃም ሆትስፐርስን 2 ለ 0 አሸንፏል። ፋቢያን ሻር እና ኒክ ዎልትማድ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

የአራተኛ ዙር ውጤቶችን ተከትሎ አርሰናል፣ ቼልሲ፣ ማንችስተር ሲቲ፣  ክሪስታል ፓላስ እና ኒውካስትል ዩናይትድ በካራባኦ ዋንጫ ለሩብ ፍጻሜ አልፋዋል።

ብሬንትፎርድ፣ ፉልሃም እና ካርዲፍ ሲቲ ትናንት ለሩብ ፍጻሜ ያለፉ ክለቦች ናቸው። 

በዚሁ መሰረት አርሰናል ከክሪስታል ፓላስ፣ ካርዲፍ ሲቲ ከቼልሲ፣ ማንችስተር ሲቲ ከብሬንትፎርድ እና ኒውካስትል ዩናይትድ ከፉልሃም በሩብ ፍጻሜው ይጫወታሉ።

የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች በታህሳስ ወር 2018 ዓ.ም ይካሄዳሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም