ቀጥታ፡

በፕሪሚየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሃዋሳ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል 

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 19/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር የሁለተኛ ቀን ውሎ ጨዋታዎች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ በአቤል ያለው ግብ ነገሌ አርሲን 1 ለ 0 አሸንፏል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ በሊጉ ሁለተኛ ድሉን ሲያስመዘግብ አዲስ አዳጊው ነገሌ አርሲ ተከታታይ ሽንፈቱን አስተናግዷል።  

በተያያዘም በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደ ጨዋታ ሃዋሳ ከተማ ወላይታ ድቻን 2 ለ 1 አሸንፏል። 

ያሬድ ብሩክ ለሃዋሳ ከተማ ግቦቹን ሲያስቆጥር ካርሎስ ዳምጠው ለወላይታ ድቻ ብቸኛዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። 

ውጤቱን ተከትሎ ሃዋሳ ከተማ በሊጉ ሁለተኛ ድሉን ሲያገኝ ወላይታ ድቻ በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

በአሁኑ ሰዓት ፋሲል ከነማ ከሲዳማ ቡና በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን በማድረግ ላይ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም