ቀጥታ፡

የኢትዮጵያን ብልፅግና አይቀሬነት ከሚያረጋግጡ ዘርፎች አንዱ ግብርና ነው-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 19/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያን ብልፅግና አይቀሬነት ከሚያረጋግጡ ዘርፎች አንዱ ግብርና በመሆኑ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ተመልክተናል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን እየተካሄደ ያለ የክረምት ስንዴ አሰባሰብ እና የበጋ ስንዴ ልማት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ መገኘታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ጠቁመዋል።


 

በዚህም የኢትዮጵያን ብልፅግና አይቀሬነት ከሚያረጋግጡ ዘርፎች አንዱ ግብርና በመሆኑ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን መመልከታቸውን ነው የገለጹት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም