ቀጥታ፡

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሶስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ 

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 19/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ውሎ ሶስት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

አዲስ አዳጊው ነጌሌ አርሲ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ከቀኑ 10 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ነጌሌ አርሲ በሊጉ እስከ አሁን ካደረጋቸው ጨዋታዎች በአንድ ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዟል። 

የ16 ጊዜ የሊጉ አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሊጉ ባደረገው አንድ ጨዋታ ሶስት ነጥብ በማግኘት አንድ ተስተካካይ መርሃ ግብር እየቀየረው ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። 

ቡድኖቹ በሊጉ ሲገናኙ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። 

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ሃዋሳ ከተማ ከወላይታ ድቻ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። 

ሃዋሳ ከተማ በሶስት ነጥብ ስምንተኛ፣ ወላይታ ድቻ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ቡድኖቹ በሁለተኛ ሳምንት ካስተናገዱት ሽንፈት በኋላ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

ምሽት 12 ሰዓት ላይ ፋሲል ከነማ ከሲዳማ ቡና በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ፋሲል ከነማ በአራት ነጥብ አራተኛ፣ ሲዳማ ቡና በስድስት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል። 

ሲዳማ ቡና ካሸነፈ የሊጉን መሪነት ዳግም ይረከባል። 

በሶስተኛ ሳምንት ኢትዮጵያ መድን ከሸገር ከተማ ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ መድን በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ከፒራሚድስ ጋር በሚያደርገው የሁለተኛ ዙር የመልስ ጨዋታ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም