ቀጥታ፡

መቻል ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር መቻል ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 3 ለ 1 አሸንፏል።

ማምሻውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ መሐመድ አበራ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ዓለምብርሃን ይግዛው ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ዩጋንዳዊው ሳይመን ፒተር በፍጹም ቅጣት ምት ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል።

ውጤቱን ተከትሎ መቻል በሊጉ ሁለተኛ ድሉን ሲያስመዘግብ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም