በሊጉ ባህር ዳር ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ምድረገነት ሽሬ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ያደረጓቸው ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል - ኢዜአ አማርኛ
በሊጉ ባህር ዳር ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ምድረገነት ሽሬ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ያደረጓቸው ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 18/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች መካሄዳቸውን እንደቀጠሉ ነው።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ባህር ዳር ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
በተያያዘም በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ምድረገነት ሽሬ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
በአሁኑ ሰዓት በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም መቻል እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛሉ።