ቀጥታ፡

የተመዘገበው ውጤት ለዘርፉ ትኩረት ከተሰጠ የትምህርት ጥራትንና ተደራሽነትን በአጭር ጊዜ ውስጥ ማሳካት እንደሚቻል ትልቅ ማሳያ ነው

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 18/2018(ኢዜአ)፦በአገር አቀፍ ደረጃ የተመዘገበው ውጤት ለዘርፉ ትኩረት ከተሰጠ የትምህርት ጥራትንና ተደራሽነትን በአጭር ጊዜ ውስጥ ማሳካት እንደሚቻል ትልቅ ማሳያ ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

በ2017 ዓ.ም አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅናና ሽልማት ተሰጠ።

ሽልማቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ከንቲባ  አዳነች አቤቤ ለተማሪዎቹ አስረክበዋል።


 

ከንቲባ አዳነች በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በከተማዋ ከፍተኛ ውጤት ከተመዘገበባቸው ዘርፎች መካከል ትምህርት አንዱ ነው።

መንግስት የትምህርት ስብራትን ለመጠገን አዲስ ፖሊሲና ሥርዓተ ትምህርት በመቅረጽ ተግባራዊ ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል።

የመማር ማስተማር ሥርዓቱን ምቹ የማድረግና የትምህርት ግብዓቶችን የማሟላት ሥራ በስፋት ሲሠራ መቆየቱን ገልጸው፤ በዚህም የተማሪዎች ውጤት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ እና እያደገ መምጣቱን አመልክተዋል።

በአገር አቀፍ ደረጃ የተመዘገበው ውጤት ለዘርፉ ትኩረት ከተሰጠ የትምህርት ጥራትንና ተደራሽነትን በአጭር ጊዜ ውስጥ ማሳካት እንደሚቻል ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።


 

በቀጣይ የመጣውን ውጤት እያበረታታን ለሌላ ስኬት ጠንክረን የምንሠራ ይሆናል ነው ያሉት።

ተማሪዎች ዛሬ የተሰጣቸው ሽልማት በቀጣይ ሕይወታቸው ጠንክረው በመስራት ለአገራቸው የበኩላቸውን የላቀ ድርሻ እንዲያበረክቱ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።


 

ዛሬ በተሰጠው እውቅና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው ታብሌት ኮምፒውተር ተበርክቶላቸዋል።

እንዲሁም ለመጣው ውጤት አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማትና የትምህርት ማኅበረሰብ እውቅና ተሰጥቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም