የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ውጭ ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ውጭ ሆነ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በ16ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ከታንዛንያ ጋር ባደረገው የመልስ ጨዋታ 1 ለ 0 ተሸንፏል።
በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዲያና ሉካስ በ16ኛው ደቂቃ ለታንዛንያ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥራለች።
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ በድምር ውጤት 3 ለ 0 ተሸንፋ ለአፍሪካ ዋንጫ ሳታልፍ ቀርታለች።
ሉሲዎቹ ዳሬሰላም ላይ በነበረው ጨዋታ 2 ለ 0 መሸነፋቸው ይታወሳል።
የምስራቅ አፍሪካዋ ሀገር ታንዛንያ እ.አ.አ በ2026 በሞሮኮ አስተናጋጅነት በሚካሄደው 16ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ መሳተፏን አረጋግጣለች።
በአፍሪካ ዋንጫው ሞሮኮን ጨምሮ 12 ሀገራት ይሳተፋሉ።