ኢትዮ ኤሌክትሪክ የሊጉ መሪ ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮ ኤሌክትሪክ የሊጉ መሪ ሆነ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሶስተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አርባምንጭ ከተማን 3 ለ 1 አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ በፍቃዱ አስረሳኸኝ፣ ሀሰን ሁሴን እና አቤል ሀብታሙ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ይገዙ ቦጋለ ለአርባምንጭ ከተማ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ውጤቱን ተከትሎ በሊጉ ሁለተኛ ድሉን ያስመዘገበው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በሰባት ነጥብ የሊጉን መሪነት ከሲዳማ ቡና ተረክቧል።
በሊጉ የመጀመሪያ ሽንፈቱን ያስተናገደው አርባምንጭ ከተማ በሁለት ነጥብ ከነበረበት 11ኛ ደረጃ ወደ 15ኛ ዝቅ ብሏል።