ቀጥታ፡

በኢትዮጵያ 63 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች የጤና መድህን ተጠቃሚ ሆነዋል

አዲስ አበባ፤ጥቅምት 18/2018(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ 63 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች በጤና መድህን ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ለሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎች ላይ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የጤና መሰረተ ልማቶችን ለማስፋት እየተሰራ ነው።

በኢትዮጵያ 63 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች በጤና መድህን ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ይህም በርካታ ዜጎች የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረጉን ገልጸው፤ በአሁኑ ወቅት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት በቀጣይ በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥሉ አብራርተዋል።

የመድሃኒት አቅርቦትን በተመለከተ ከውጭ የሚገቡ መድሃኒቶች ለመቀነስና በአገር ምርቶች ለመተካት ሙከራ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

የጤናውን ዘርፍ ለማስፋትና የህዝቦችን የጤና አገልግሎት ፍላጎት ለማሟላት እየተሰራ መሆኑንም አብራርተዋል።

ለአብነትም የቅዱስ ጵውሎስ ሆስፒታል አንድ ሺህ አልጋ ያለው የመሰረተ ልማት ግንባታ ማደረጉን ገልጸው፤በቀጣይ አስፈላጊው ግብዓት ተሟልቶ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚደረግ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም