ኢትዮጵያ ውስጥ 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ወጣቶች በነጻ የኮዲንግ ስልጠና ወስደዋል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ውስጥ 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ወጣቶች በነጻ የኮዲንግ ስልጠና ወስደዋል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ውስጥ 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ወጣቶች በነጻ የኮዲንግ ስልጠና መውሰዳቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ ወቅት ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዲጂታላይዜሽንን በሚመለከት በሰጡት ማብራሪያ ኢትዮጵያ ውስጥ 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ወጣቶች በነጻ የኮዲንግ ስልጠና ወስደዋል ብለዋል።
ይህ ትልቅ ቁጥር መሆኑን ጠቁመው 93 ሚሊዮን ደንበኞች ደግሞ የቴሌኮም አገልግሎት ተጠቃሚ ሲሆኑ 55 ሚሊዮን ዜጎች የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚ መሆን ችለዋል ሲሉም ገልጸዋል።
ይህ ኢትዮጵያን ዲጂታላይዝ ለማድረግ የጀመረነው ስራ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ መሆኑን አመላካች ነው ሲሉክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናግረዋል።