ቀጥታ፡

ምክር ቤቱ የቀረበለትን የድጋፍ ሞሽን አፀደቀ

አዲስ አበባ፤ጥቅምት 18/2018(ኢዜአ)፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም በፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ የቀረበውን የ2018 የመንግሥት የትኩረት አቅጣጫ የድጋፍ ሞሽን አፅድቋል።

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ አካሂዷል።


 

በፕሬዝዳንቱ የቀረበውን ሞሽን መነሻ በማድረግ ከምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

ምክር ቤቱም የቀረበለትን የድጋፍ ሞሽን አፅድቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም