ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያስፈልገው ብቸኛው መንገድ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያስፈልገው ብቸኛው መንገድ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያስፈልገው ብቸኛው መንገድ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አስገነዘቡ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰላምና ጸጥታን በሚመለከት በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያስፈልገው ብቸኛው መንገድ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ነው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን እድገት የማይሹ ሀገራት በጦርነት እንደማያሸንፉን ያውቁታል ያላቸው ምርጫ ባንዳዎችን መላክ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያን በቅጡ ያላወቁ የውስጥ ባንዳዎች ደግሞ ከጠላት ጋር በማበር ዓላማቸውን የሚያሳኩ ይመስላቸዋል ይህ ፈጽሞ ሊሳካ አይችልም ነው ያሉት።
ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያስፈልገው ብቸኛው መንገድ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግስት ችግሮች አሉኝ የሚሉ አካላት ጋር ቁጭ ብሎ በመነጋገር ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አሁንም ክፍት ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያስፈልገው ብቸኛው መንገድ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ነው ሲሉም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስገነዘቡት።