በደሴ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተዘጋጀ - ኢዜአ አማርኛ
በደሴ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተዘጋጀ
ደሴ ፤ ጥቅምት 18/2018(ኢዜአ)፡- በደሴ ከተማ አስተዳደር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ ተደረገ።
ማዕከሉ 16 ተቋማት እና ከ70 በላይ የአገልግሎት ዘርፎች የተመቻቹ ሲሆን፤ ይህም ብልሹ አሰራርን በማስቀረት ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እንደሚሰጡ ተመላክቷል።
ለአገልግሎት አሰጣጡ ምቹ እንዲሆን በቴክኖሎጂ የተደገፈ የሲስተም ዝርጋታ ስራው የተሳካ ስለመሆኑ በተደረገው የሙከራ ትግበራ ማረጋገጥ ተችሏል።
ለከተማው ማህበረሰብ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት በቅርብ ቀናት ወደ ተሟላ ስራ እንደሚገባ ተጠቁሟል።
የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝን ጨምሮ ሌሎች የከተማ አመራር አባላትና ባለድርሻ አካላት መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከሉን ተመልክተዋል።