በሁሉም መስፈርት የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም ስብራቶችን የጠገነበት ፍጥነትና ያስገኘው ውጤት አስደማሚ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
በሁሉም መስፈርት የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም ስብራቶችን የጠገነበት ፍጥነትና ያስገኘው ውጤት አስደማሚ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2018(ኢዜአ)፡-በሁሉም መስፈርት የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም ስብራቶችን የጠገነበት ፍጥነትና ያስገኘው ውጤት አስደማሚ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ÷ የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ያነገባቸውን ዓላማዎችና ያስገኛቸውን ውጤቶችን አብራርተዋል።
የሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የኢትዮጵያ የመጠባበቂያ ክምችት ከአስር ዕጥፍ በላይ ዕድገት እንዲያስመዘግብ ማስቻሉን አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ ባለፈው በጀት ዓመት ትልቅ የሚባልና በዓለም ላይ በጣት ከሚቆጠሩ አራትና አምስት ሀገራት ባደጉበት የዕድገት ደረጃ ማደጓን አስረድተዋል።
የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት በተሰራው ስራም በርካታ ኢንቨስተሮች ወደሀገር ቤት እየመጡ መሆኑን አንስተዋል።
የሀገር ውስጥ አልሚዎችም ሃብታቸውን በተቀናጀ መንገድ ኢትዮጵያ ውስጥ ማፍሰስ እንዲችሉ የተሰሩ ሰፋፊ ተግባራት ውጤት አምጥተዋል ነው ያሉት።
በሁሉም መስፈርት ሲታይ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም ስብራቶችን የጠገነበት ፍጥነትና ያስገኘው ውጤት አስደማሚ ተብሎ የሚወሰድ መሆኑን አስረድተዋል።