ቀጥታ፡

ያለፈው በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በታሪኳ ከፍተኛ ገቢ ያገኘችበት ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2018(ኢዜአ)፦ ያለፈው በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በታሪኳ ከፍተኛ ገቢ ያገኘችበት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገቢን በተመለከተ ለተነሳላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ ያለፈው በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በታሪኳ ከፍተኛ ገቢ ያገኘችበት ነው ብለዋል።

ለአብነትም ከሸቀጦች ወጪ ንግድ 8 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱን በመጥቀስ።

እንዲሁም ከሬሚታንስ 7 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ መገኘቱንና ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካትም በቢሊዮን ዶላር ማዳን ተችሏል ነው ያሉት።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው የኢትዮጵያ ሪዘርቭ በ10 እጥፍ አድጓል ሲሉም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም