የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርም በሁሉም መመዘኛዎች ከፍተኛ ለውጥ በፍጥነት ማስመዝገብ ችሏል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርም በሁሉም መመዘኛዎች ከፍተኛ ለውጥ በፍጥነት ማስመዝገብ ችሏል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርም በሁሉም መመዘኛዎች ከፍተኛ ለውጥ በፍጥነት ማስመዝገብ ችሏል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አስታወቁ።
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግብርናን በተመለከተ ለተነሳላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርም በሁሉም መመዘኛዎች ከፍተኛ ለውጥ በፍጥነት ማስመዝገብ ችሏል ብለዋል።
ግብርና ብቻውን የ7 ነጥብ 3 በመቶ እድገት ማስመዝገቡንም ለአብነት አንስተዋል።
በምርት ደረጃም ሩዝ ከነበረበት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ወደ 63 ሚሊዮን ኩንታል ማሳደግ የተቻለ ሲሆን የስንዴ ምርትም ከለውጡ በፊት ከነበረበት 47 ሚሊዮን ኩንታል ወደ 280 ሚሊዮን ኩንታል በአጠረ ጊዜ ውስጥ አሳድገነዋል ብለዋል።